ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ።
ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።
ተነሥተው ምድርን እንዳይወርሱ፣ ዓለምንም በከተሞቻቸው እንዳይሞሉ፣ ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት፣ ወንድ ልጆቹ የሚታረዱበትን ስፍራ አዘጋጁ።
እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ መበለትነትና የወላድ መካንነት፣ አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤ የቱን ያህል አስማት፣ የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣ በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።
በአንቺ ወንዱንና ሴቱን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ሽማግሌውንና ወጣቱን እሰባብራለሁ። በአንቺ ጐረምሳውንና ኰረዳዪቱን እሰባብራለሁ።
ሴቶች በጽዮን፣ ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።
ሰልማን፣ ቤትአርብኤልን በጦርነት ጊዜ እንዳፈራረሰ፣ እናቶችንም ከልጆቻቸው ጋራ በምድር ላይ እንደ ፈጠፈጣቸው፣ ሽብር በሕዝብህ ላይ ይመጣል፤ ምሽጎችህም ሁሉ ይፈራርሳሉ።
ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ ተሰድዳም ሄደች። በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤ በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።