እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጕድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።
የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
ብርሽ ዝጓል፣ ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤
ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣ እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቅቃቸው፣ የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣ በዚያ ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ ይህም ኀጢአቱ የመወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።
ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።
ርሳሱን ለማቅለጥ፣ ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።
መኖሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፤ ከሽንገላቸውም የተነሣ ሊያውቁኝ አልፈቀዱም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?
በእኔ ላይ ያመፁትንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ ከሚኖሩበት አገር አወጣቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ሁላችሁም የብረት ዝቃጭ ስለ ሆናችሁ ወደ ኢየሩሳሌም እሰበስባችኋለሁ።
ሰው ብርንና መዳብን፣ ብረትንና እርሳስን እንዲሁም ቈርቈሮን ለማቅለጥ በከውር ውስጥ አስገብቶ እሳት እንደሚያነድድበት፣ እኔም እንደዚሁ በቍጣዬና በመዓቴ ወደ ከተማዪቱ እሰበስባችኋለሁ፤ በዚያም አቀልጣችኋለሁ።
ብር በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፣ እናንተም በከተማዪቱ ውስጥ ትቀልጣላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።’ ”
በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ ቀን አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ ከእንግዲህ ወዲያ፣ በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።
ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ቍርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤
መንሹ በእጁ ነው፤ ዐውድማውን ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውን በጐተራ ይከትታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።
እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።