በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋራ ታገለ።
ከዚያም ወንድሙ ተወለደ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ከዚህም የተነሣ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ርብቃ ልጆቿን ስትወልድ፣ ይሥሐቅ የስድሳ ዓመት ሰው ነበር።
ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ የይሁዳ ነገድ ብቻ ሲቀር እስራኤልን ከፊቱ አራቀ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ተዋቸው፤ አስጨነቃቸው፤ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸውም ድረስ በማራኪዎቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።
“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር።
አሁንም መጨረሻሽ ደርሷል፤ ቍጣዬን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፤ እንደ አካሄድሽ እፈርድብሻለሁ፤ ስለ ጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ።
እነሆ፤ መዓቴን በቅርብ ቀን አፈስስብሻለሁ፤ በአንቺ ላይ ቍጣዬን እፈጽምብሻለሁ፤ እንደ አካሄድሽ እፈርድብሻለሁ፤ ስለ ጸያፍ ተግባርሽም ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።
“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል።
መንትዮቹ ገና ሳይወለዱ፣ ወይም በጎም ሆነ ክፉ ሳያደርጉ፣ የእግዚአብሔር ሐሳብ በምርጫ ይጸና ዘንድ፣