Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሆሴዕ 12:1

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።

ከዚያም የአሦር ንጉሥ ፎሓ ምድሪቱን ወረረ፤ ምናሔም ርዳታውን ለማግኘትና በመንግሥቱ ላይ ያለውን ይዞታ ለማጽናት ሲል፣ አንድ ሺሕ መክሊት ብር ሰጠው።

ከዚህም በላይ በይሁዳ ኰረብቶች ላይ መስገጃ ስፍራዎች ሠርቶ የኢየሩሳሌም ሕዝብ በዚያ እንዲያመነዝር አደረገ፤ ይሁዳንም አሳተ።

“ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል?

ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤ በአንደበታቸው ዋሹት።

መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ ለምን ትሮጫለሽ? አሦር እንዳዋረደሽ፣ ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል።

እረኞችሽ ሁሉ በነፋስ ይወሰዳሉ፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ ከክፋትሽም ሁሉ የተነሣ፣ ታፍሪያለሽ፤ ትዋረጂያለሽም።

ወንድሞቻችሁ የሆኑትን፣ የኤፍሬምን ሁሉ ሕዝብ እንዳስወገድሁ፣ እናንተንም ከፊቴ እጥላችኋለሁ።’

እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ ለአሦርና ለግብጽ እጃችንን ሰጠን።

በሌላ ስፍራ ቢተከልስ ይጸድቅ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲመታውስ ባደገበት ስፍራ ፈጽሞ አይደርቅምን?’ ”

ኤፍሬም በሐሰት፣ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ለአምላክ የማይገዛ፣ የታመነውን ቅዱሱን የሚቃወም ነው።

የቍጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤ እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ ሰው አይደለሁምና፣ በቍጣ አልመጣም።

“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣ ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ። “ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብላችሁም አትማሉ።

ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።”

“ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቍስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

“ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣ አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤ አንድ ጊዜ ወደ ግብጽ ይጣራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።

“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች