ስለዚህ የመጀመሪያው ኪዳን እንኳ ያለ ደም የጸና አልነበረም።
ከዚያም ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል በመውሰድ፣ በሳሕን ውስጥ ካለው ደም ነክራችሁ የየቤቶቻችሁን ጕበንና ግራ ቀኝ መቃኑን ቀቡ። ከእናንተ አንድም ሰው እስኪነጋ ድረስ ከቤቱ አይውጣ።
የአሮንንም ልጆች ወደ ፊት ጠራ፤ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ የቀኝ ጆሯቸውን ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣትና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት አስነካ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።
በዘላለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እንድናመልክ ኅሊናችንን ከምውት ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!
ምክንያቱም ኑዛዜው የሚጸናው ሰውየው ሲሞት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ተናዛዡ በሕይወት እስካለ ድረስ ኑዛዜው ዋጋ አይኖረውም።
ሙሴ እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፣ ከቀይ የበግ ጠጕርና ከሂሶጵ ጋራ ወስዶ፣ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤
በርግጥ ከጥቂት ነገሮች በቀር ሁሉም ነገር በደም መንጻት እንዳለበት ሕጉ ያዝዛል፤ ደም ሳይፈስስ ስርየት የለምና።