ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብጽ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?
እነርሱ ግን በምድረ በዳ በልዑል ላይ በማመፅ፣ በርሱ ላይ ኀጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ።
በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት! በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት!
ከተማዪቱን የሚወጓት ባቢሎናውያን ወደ ውስጥ ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤ ያስቈጡኝ ዘንድ ሕዝቡ በየሰገነቱ ላይ ለበኣል ያጠኑባቸውንና ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያቀረቡባቸውን ቤቶች ጭምር ያነድዳሉ።
ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።
ልትኖሩባት በመጣችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠን፣ እጆቻችሁ ባበጇቸው ነገሮች ለምን ታስቈጡኛላችሁ? በምድር ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የርግማንና የመዘባበቻ ምልክት ለመሆን ራሳችሁን ታጠፋላችሁን?
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? እነዚህን ሁሉ ታምራት በመካከሉ እያደረግሁ የማያምንብኝስ እስከ መቼ ነው?
እስራኤላውያን በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሏቸው፤ “ምነው በግብጽ ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን ባረፍነው ኖሮ!
አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል።
መኖሪያችሁ እንድትሆን በጽኑ ወደማልሁላችሁ ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡባትም።
ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከተላኩት ሰዎች በሕይወት የተረፉት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ ነበሩ።
እርስ በርሳቸውም፣ “አለቃ መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ።
ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።
ረዳትህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ይገባባታል፤ ምድሪቱን እንዲወርሱ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ፣ አበረታታው።
ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወድዳለሁ።