በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና።
አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤ በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ ብፁዕ ነው፤
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
የሰው ደም ያለበት ሰው፣ ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ ማንም ሰው አይርዳው።
“እናንተ ቀስት የምትገትሩ ሁሉ፣ በባቢሎን ዙሪያ ተሰለፉ፤ አንዳች ሳታስቀሩ ፍላጾችን ስደዱባት፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታለችና።
እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣ ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣ ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣ በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።
“በጽዮን ላይ ስላደረሱት ጥፋት ሁሉ ለባቢሎንና በባቢሎን ለሚኖሩት ሁሉ ዐይናችሁ እያየ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
ንግድህ ስለ ደረጀ፣ በዐመፅ ተሞላህ፣ ኀጢአትም ሠራህ፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ በውርደት አሳደድሁህ፤ ጠባቂ ኪሩብ ሆይ፤ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አስወጣሁህ።
ወደ ጕድጓድ ከሚሄዱት ጋራ ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ።
ግብጽ ባድማ፣ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ፣ በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና።
ታዲያ መረቡን ባለማቋረጥ መጣል፣ ሕዝቦችንስ ያለ ርኅራኄ መግደል አለበትን?
አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል።
ሊባኖስ ሆይ፤ እሳት ዝግባሽን እንዲበላው ደጆችሽን ክፈቺ!