Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዕንባቆም 2:12

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚሠራ፣ በወንጀልም ለሚመሠርታት ወዮለት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቤቴል ሰው አኪኤል፣ በአክዓብ ዘመን ኢያሪኮን መልሶ ሠራት። እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ መሠረቷን ሲያኖር በኵር ልጁ አቢሮን ሞተ፤ የቅጽር በሮቿንም በሚሠራበት ጊዜ የመጨረሻው ልጁ ሠጉብ ሞተ።

“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት! እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።

ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምን በክፋት የምትገነቡ፤ ስሙ።

ለደም ከተማ ወዮላት! ሐሰት፣ ዘረፋም ሞልቶባታል፤ ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም።

“ታዲያ በእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ላይ በማፌዝና በመዘበት እንዲህ እያሉ ሁሉም አይሣለቁበትምን? “ ‘የራሱ ያልሆነውን ለራሱ ለሚያከማች፣ ራሱን በዐመፅ ባለጠጋ ለሚያደርግ ወዮለት! ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል?’

እንግዲህ፣ እኛንም እናንተንም በክርስቶስ ጸንተን እንድንቆም የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፤ የቀባንም እርሱ ነው፤

በዚያ ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህች ከተማ ኢያሪኮን መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤ “መሠረቷን ሲጥል፣ የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣ የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።

ሴቲቱንም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች