ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።”
እንዲሁም ከእናንተ ጋራ ከነበሩት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ከወፎች፣ ከቤት እንስሳት፣ ከዱር እንስሳት፣ ከእናንተ ጋራ ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።
ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።
መከራህን ትረሳለህ፤ ዐልፎ እንደ ሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።
“ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣ እንደ ኖኅ ዘመን ነው፤ አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቈጣ፣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።
እንግዲህ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የሚጠፋ ከሆነ፣ እናንተ እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል? አዎን፣ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልትኖሩ ይገባችኋል፤
በዚያው ቃል ደግሞ አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር፣ ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።