ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።
እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል።
ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።”
ተባዕትና እንስት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ መርከቧ ገቡ።
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።
ኖኅ ወደ መርከቡ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር፤ የጥፋትም ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው።