ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤
አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት ብላ ጠራችው።
ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።
አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
የሄኖስ ልጅ፣ የሤት ልጅ፣ የአዳም ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ።