“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።
ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣ የአጥፊ ወንድም ነው።
የስምዖን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የስምዖንን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
ከስምዖን ነገድ፣ የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፤
ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው።
ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣