መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከዐምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፤ ከዐምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።”
ጠላቶችህን አሳልፎ በእጅህ የሰጠህ፣ ልዑል አምላክ ይባረክ።” አብራምም ከሁሉ ነገር ዐሥራትን አውጥቶ ሰጠው።
የሰዶም ንጉሥም አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።
ይህ ሐውልት አድርጌ ያቆምሁት ድንጋይ፣ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሀብት ሁሉ፣ ከዐሥር እጅ አንዱን ለአንተ እሰጣለሁ።”
እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ ዐምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም።
ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ።
እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን፣ ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት።
ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።
ብፁዕ ነው፤ ለድኾች የሚያስብ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።
“ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራት የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነው።
ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
“በመገናኛው ድንኳን በሚያገለግሉበት ጊዜ ለሚሠሩት ሥራ ደመወዝ እንዲሆናቸው ከእስራኤል የሚወጣውን ዐሥራት ሁሉ ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።
በየዓመቱ ከዕርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ።
የዐሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ምርት አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፣ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፤