የአሴር ልጆች፦ ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሔቤርና መልኪኤል ናቸው፤
ልያም፣ “ምንኛ ደስተኛ ሆንሁ ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛዋ ይሉኛል” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት።
የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድ፣ አሴር ናቸው። እነዚህ ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች ነበሩ።
እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።
“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።
ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።
ከአሴር የኤክራን ልጅ ፋግኤል፤
ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤ በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።