ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል፣ እንዲሁም ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው።
አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ፣ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አረጋዊ አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤
በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፣ ብሩንም በእያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጕዟቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፣
እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቾቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደ ተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።
ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋራ ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ ዐብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።
ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤
ከግብጽ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው “እስኪ እንደ ገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።
ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋራ ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።
እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፉንና ርዳታውን፣ የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤