ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በሁለቱም ሹማምቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤
ከዚህም በኋላ የግብጽ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊና እንጀራ ቤቱ ጌታቸውን የግብጽን ንጉሥ በደሉት።
የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር።
የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው እንጂ።
በአንድ ወቅት ፈርዖን እኔንና የእንጀራ ቤት አዛዡን ተቈጥቶ በዘበኞቹ አለቃ ግቢ አስሮን ነበር።
ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።
ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።
የንጉሥ ቍጣ የሞት መልእክተኛ ነው፤ ጠቢብ ሰው ግን ቍጣውን ያበርዳል።
የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ በፊቱ ሞገስ ማግኘትም በሣር ላይ እንዳለ ጠል ነው።
ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።
ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
እርሱም ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎች ጋራ ጥለኛ ነበር፤ አገራቸው ምግብ የሚያገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበር፣ የንጉሡን ባለሟል የብላስጦስን ድጋፍ ካገኙ በኋላ፣ አንድ ላይ ሆነው ከንጉሡ ጋራ ለመታረቅ ጠየቁ።