“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና ዐብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።
“ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም መልሳ፣ “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።
ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሿን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች።
ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
“በሕያውነቴ እምላለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር “የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የቀለበት ማኅተም ብትሆን እንኳ ኖሮ፣ አውልቄ እጥልሃለሁ፤
ለአመንዝራነት፣ ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤ በእነዚህም የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ።
“ ‘ከምራትህ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከርሷም ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ።
“አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤