ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “ብላቴናው ጕድጓድ ውስጥ የለም፤ የት አባቴ ልሂድ?” አለ።
ኑ እንግደለውና ከጕድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስኪ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን!”
እነርሱ ግን መልሰው፣ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን፣ አንዱ ግን የለም” አሉት።
እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን፣ ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ የለም፤ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋራ በከነዓን ይገኛል።’
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ ከራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።”