ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።
ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።
የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማዪቱም ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
በኣልሐናን ሲሞት ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የእርሱም ከተማ ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የማጥሬድ ልጅ ነበረች።
ጌድራዊው በአልሐናን በምዕራባዊው ኰረብቶች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ።