የዓና ልጆች፦ ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ፤
የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ።
የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦ አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣
የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።
የዲሶን ወንዶች ልጆች፦ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን፤
እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሐምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን።