በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣
የሖሪ ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይር በረሓማ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ድረስ ድል አደረጓቸው።
እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣
ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
ሖሪውያን ቀድሞ በሴይር ይኖሩ ነበር፤ የዔሳው ዘሮች ግን ከዚያ አሳድደው አስወጧቸው። እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሰጠው ምድር ላይ እስራኤል እንዳደረገው ሁሉ፣ እነዚህም ሖሪውያንን ከፊታቸው አጥፍተው መኖሪያቸውን እዚያው አደረጉ።
እግዚአብሔር ሖሪውያንን ከፊታቸው ባጠፋ ጊዜ፣ በሴይር ለሚኖሩት የዔሳው ዘሮች ያደረገው ይህንኑ ነበር። እነርሱም አሳድደው በማስወጣት ባስለቀቁት ስፍራ ላይ እስከ ዛሬ ይኖራሉ።