የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤
የዔሳው ወንዶች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ቲምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ።
ስለ ኤዶም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቷልን? ምክር ከአስተዋዮች ርቋልን? ጥበባቸውስ ተሟጧልን?
“ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤ በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ ተገድሎ ይጠፋል።