ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብታቸው ንብረታቸው፣ እንስሶቻቸው ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን? ስለዚህ ባሉት እንስማማ፤ እነርሱም ዐብረውን ይኑሩ።”
ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋራ እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው ዐብረውን ለመኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደ ሆነ ብቻ ነው።
ከከተማዪቱ በር ውጭ የተሰበሰቡት ሁሉ በኤሞርና በልጁ በሴኬም ሐሳብ ተስማሙ፤ በከተማዪቱም ያሉት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ።
ታማኝ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ከቅጣት አያመልጥም።
ርግብ ሻጮችንም፣ “እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” አላቸው።