ሰውየውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ።
በዚያ ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለ ሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።
ሰውየውም፣ “ከእግዚአብሔርም፣ ከሰዎችም ጋራ ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ፣ ያዕቆብ አይባልም” አለው።
እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበረ፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።
የልጁ እናት ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፤ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው፤ ስለዚህ ተነሥቶ ተከተላት።
ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤ የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሸሸ፤ እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤ ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ።