ደግሞም ምጽጳ ተባለ፤ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሏልና፤ “እኛ በተለያየን ጊዜ፣ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ታዛቢ ሆኖ ይቁም።
ንጉሥ አሳ አንድም ሰው እንዳይቀር በይሁዳ ሁሉ ዐዋጅ አስነገረ፤ ከዚያም ሕዝቡ ባኦስ በራማ ሲሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት አጋዘ፤ በእነርሱም ንጉሡ አሳ የብንያምን ጌባዕና ምጽጳን ሠራበት።
“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ አድምጡ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።
አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፣ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋራ ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ደገመው።
ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ። ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው።
አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ እግዚአብሔር በመካከላችን ለዘላለም ምስክር ነው።”