ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች።
ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ራሔል ነበር።
ልያም፣ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ክሶኛል” አለች፤ ስሙንም ይሳኮር ብላ አወጣችለት።
እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ ዐድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት፣ ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል”። አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው።
የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤
የዛብሎን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የይሳኮርን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤