Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፍጥረት 30:16

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያች ምሽት ያዕቆብ ከዕርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለ ተከራየሁህ የዛሬው ዐዳርህ ከእኔ ጋራ ነው” አለችው፤ ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከርሷ ጋራ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስንዴ በሚታጨድበት ወቅት፣ ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ፤ እንኮይም አግኝቶ ለእናቱ ለልያ አመጣላት። ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።

ልያም፣ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለ ልጅሽ እንኮይ ዛሬ ከአንቺ ጋራ ይደር” አለቻት።

እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ዐምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች