እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና፣
“ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ።
እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጕዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና” አለው።
የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤
እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።
ለጥቂት ጊዜ እዚሁ አገር ተቀመጥ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ ለአብርሃም በመሐላ የገባሁለትን ቃል አጸናለሁ።
ይኸውም አብርሃም ቃሌን ሰምቶ፣ ድንጋጌዬን፣ ትእዛዜን፣ ሥርዐቴንና ሕጌን በመጠበቁ ነው።”
ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ።
ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም።
“እጆች ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተዘርግተዋልና፤ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋቸዋል” አለ።
እግዚአብሔርም የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ የገባውንም ቃል ኪዳን ዐሰበ።
ለባሪያዎችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለእስራኤል፣ ‘ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ለዘርህም ተስፋ አድርጌ የሰጠኋቸውን ይህችን ምድር ሁሉ እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለምም ርስታቸው ትሆናለች’ በማለት በራስህ የማልኸውን አስታውስ።”
ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል።
ነገር ግን እነዚህን ትእዛዞች ባትጠብቁ፣ ይህ ቤተ መንግሥት እንዲወድም በራሴ ምያለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።’ ”
በግብጽ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብጽ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤
ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፤ እንደ አንበጣ መንጋ በሆነ ብዙ ሰው አጥለቀልቅሻለሁ፤ እነርሱም በድል አድራጊነት በላይሽ ያቅራራሉ።
“ ‘ዳግመኛም በአጠገብሽ በማልፍበት ጊዜ ወደ አንቺ ተመለከትሁ፤ ለመፈቀርም እንደ ደረስሽ ባየሁ ጊዜ፣ የመጐናጸፊያዬን ዘርፍ በላይሽ ዘርግቼ ዕርቃንሽን ሸፈንሁ። ማልሁልሽ፤ ከአንቺም ጋራ ቃል ኪዳን ተጋባሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ አንቺም የእኔ ሆንሽ።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል እንደ ገባህላቸው፣ ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም ምሕረትን ታደርጋለህ።
ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማሰብ፣