መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።
የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።
ከዚያም በለዓም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች። ‘ና ያዕቆብን ርገምልኝ፤ መጥተህም እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።