ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣
ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣
የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ፤ የድዳንም ልጆች፦ አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ናቸው።
የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና እና ከእግዚአብሔር ስም ጋራ ያለውን ግንኙነት በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው መጣች።
“ ‘ካራን፣ ካኔ፣ ዔድን፣ የሳባ ነጋዴዎች፣ አሦርና ኪልማድ ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር።