Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፍጥረት 1:21

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።

እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ። መሸ፤ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን።

እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ።

ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።

ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ።

እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ፣ ከአንተ ጋራ ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።”

እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።

አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታትና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል።

እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”

“እስኪ እንስሳትን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤

“ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣ የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው።

በላዬ ጠባቂ ታደርግ ዘንድ፣ እኔ ባሕር ነኝን ወይስ የባሕር አውሬ?

የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እየተዋለዱ በዙ፤ ቍጥራቸው እጅግ ከመጨመሩም የተነሣ የግብጽን ምድር ሞሏት።

አባይ በጓጕንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ ዐልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሖቃዎችህ ይገባሉ።

“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ “ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣ በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤ በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።

እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዐደረ።

እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፤ ዮናስንም በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።

ዮናስ በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ቈየ፣ እንዲሁ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ ይቈያል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች