ከዚያም ከሦስት ዓመት በኋላ፣ ኬፋን አገኘው ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ ከርሱም ጋራ ዐሥራ ዐምስት ቀን ተቀመጥሁ።
ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመለከተውና፣ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው፤ “ኬፋ” ማለት ጴጥሮስ ማለት ነው።
ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ በግልጽ ስቶ ስለ ነበር፣ ፊት ለፊት ተቃወምሁት።
ተግባራቸው እንደ ወንጌል እውነት አለመሆኑን በተረዳሁ ጊዜ፣ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፤ “አንተ አይሁዳዊ ነህ፤ ሆኖም በአሕዛብ ሥርዐት እንጂ በአይሁድ ሥርዐት አትኖርም፤ ታዲያ አሕዛብ የአይሁድን ሥርዐት እንዲከተሉ እንዴት ታስገድዳቸዋለህ?
ነገር ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን እንዲሰብክ ዐደራ እንደ ተሰጠው፣ እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን እንድሰብክ ዐደራ እንደ ተሰጠኝ ተገነዘቡ፤
እንደ አዕማድ የሚቈጠሩት ያዕቆብ፣ ኬፋና ዮሐንስም የተሰጠኝን ጸጋ ባስተዋሉ ጊዜ፣ ለእኔና ለበርናባስ የትብብር ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ ከዚያም እኛ ወደ አሕዛብ፣ እነርሱ ደግሞ ወደ አይሁድ እንድንሄድ ተስማሙ።