ኢየሩሳሌምም ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ዐረፍን።
በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።
እኔም ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም ሦስት ቀን ከቈየሁ በኋላ፣