Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዕዝራ 8:15

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም ወደ አኅዋ በሚፈስሰው ወንዝ አጠገብ ሰዎቹን ሰበሰብኋቸው፤ በዚያም ሦስት ቀን ቈየን። ሕዝቡንና ካህናቱን ስመለከት፣ ከሌዊ ወገን የሆነ አንድም ሰው በዚያ አላገኘሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም በካህናቱ፣ በሌዋውያኑ፣ በመዘምራኑ፣ በበር ጠባቂዎቹ፣ በቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ወይም በሌሎቹ በዚህ በእግዚአብሔር ቤት ሠራተኞች ላይ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻ ለመጣል ሥልጣን እንደሌላችሁ ይህን ዕወቁ።

እንዲሁም በንጉሡ፣ በአማካሪዎቹና በኀያላን ሹሞቹ ፊት ሁሉ ሞገስን የሰጠኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። የአምላኬ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ስለ ነበረች፣ ዐብረውኝ እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል የታወቁ ሰዎችን ለመሰብሰብ ብርታት አገኘሁ።

እንደዚሁም አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ከካህናት፣ ከሌዋውያን፣ ከመዘምራን፣ ከበር ጠባቂዎችና ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ጋራ በመሆን በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሰባተኛው ዓመት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

ከበጉዋይ ዘሮች ዑታይና ዘቡድ፣ ከእነርሱም ጋራ 70 ወንዶች።

ስለዚህ መራሕያኑን አልዓዛርን፣ አርኤልን፣ ሸማያን፣ ኤልናታንን፣ ያሪብን፣ ኤልናታን፣ ናታንን፣ ዘካርያስንና ሜሱላምን እንዲሁም መምህራኑን ዮያሪብንና ኤልናታንን አስጠራኋቸው፤

ከፊንሐስ ዘሮች ጌርሶን፤ ከኢታምር ዘሮች ዳንኤል፤ ከዳዊት ዘሮች ሐጡስ፤

ራሳችንን በአምላካችን ፊት ዝቅ እንድናደርግ፣ ጕዞውም ለእኛና ለልጆቻችን፣ ለንብረታችንም ሁሉ የተቃና እንዲሆንልን፣ እዚያው በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅሁ።

እኛም በመጀመሪያው ወር ዐሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን። የአምላካችን እጅ በላያችን ነበረች፤ እርሱም ከጠላቶቻችንና በመንገድ ላይ ከሚሸምቁ አዳነን።

በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

በሠላሳኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን፣ በኮቦር ወንዝ አጠገብ በምርኮኞች መካከል ሳለሁ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።

ከዚያም በኮቦር ወንዝ አጠገብ በቴልአቢብ ወደሚኖሩት ምርኮኞች መጣሁ፣ በድንጋጤ ፈዝዤም ከእነርሱ ጋራ ሰባት ቀን በመካከላቸው ተቀመጥሁ።

በሰንበት ቀንም፣ የጸሎት ስፍራ በመፈለግ፣ ከከተማዪቱ በር ወጥተን ወደ አንድ ወንዝ ወረድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች