የላካችሁልኝ ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነብቧል።
ንጉሡም ይህን መልስ ላከ፤ ለአገረ ገዥው ሬሁም፣ ለጸሓፊው ሲምሳይ፣ በሰማርያና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚኖሩ ተባባሪዎቻቸው፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤
እኔም ትእዛዝ ሰጥቼ ምርመራ ተደርጓል፤ በምርመራውም መሠረት ይህች ከተማ ከጥንት ጀምሮ በነገሥታት ላይ ስታምፅ የኖረች የዐመፅና የወንጀል መናኸሪያ እንደ ሆነች ማስረጃ ተገኝቷል።
ሕዝቡ የሚነበበውን ማስተዋል እንዲችሉ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ካነበቡላቸው በኋላ ይተረጕሙላቸውና ይተነትኑላቸው ነበር።