ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የመጡ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392
የዳላያ፣ የጦብያና የኔቆዳ ዘሮች 652
ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤