የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223
ከዚያም ተነሥቶ ከቤቴል በስተምሥራቅ ወዳሉት ተራሮች ሄደ፤ ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምሥራቅ አድርጎ ድንኳን ተከለ፣ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ጸለየ።
የማክማስ ሰዎች 122
የናባው ዘሮች 52
የሌላው ናባው ሰዎች 52
“ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤ የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋራ፣ ተማርኮ ይወሰዳልና፣ በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።
የቤቴል ሰዎች እግዚአብሔርን ለመለመን ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ዐብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጋራ ላኩ፤
ኢያሱ ከቤቴል በስተምሥራቅ ካለችው ከቤትአዌን አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ልኮ፣ “ወደዚያ ውጡ፤ አገሪቱንም ሰልሉ” አላቸው፤ ሰዎቹም ወጥተው ጋይን ሰለሉ።
እስራኤልን ለማሳደድ ከጋይና ከቤቴል ያልወጣ ወንድ አልነበረም፤ ከተማዪቱንም ከፍተው ትተው እስራኤልን ማሳደድ ያዙ።
ከዚያም ኢያሱ ሰዎቹን ላካቸው፤ እነርሱም ሄደው ከጋይ በስተምዕራብ በቤቴልና በጋይ መካከል ባለው ቦታ አደፈጡ፤ ኢያሱ ግን እዚያው ከሕዝቡ ጋራ ዐደረ።