ከሌዋውያኑም መካከል፤ ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።
ከፋስኮር ዘሮች፤ ኤልዮዔናይ፣ መዕሤያ፣ ይስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባትና ኤልዓሣ።
ከመዘምራኑም መካከል፤ ኤልያሴብ። ከበር ጠባቂዎቹም፣ ሰሎም፣ ጤሌም፣ ኡሪ።
በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።
ወንድሞቻቸው፦ ሰበንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን፣
እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት የውጩ ሥራ ኀላፊዎች የነበሩት፣ ከሌዋውያን አለቆች ሁለቱ ሳባታይና ዮዛባት።
ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን፣ ፌልያ ሕዝቡ በዚያው ቆመው እንዳሉ ሕጉን አስረዷቸው።