ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።
ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋራ በተወሰነው ቀን ይምጡ።”
ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤
ከባኒ ዘሮች፤ ሜሱላም፣ መሉክ፣ ዓዳያ፣ ያሱብ፣ ሸዓልና ራሞት።
መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዚር፣
እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት የውጩ ሥራ ኀላፊዎች የነበሩት፣ ከሌዋውያን አለቆች ሁለቱ ሳባታይና ዮዛባት።
የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣
አሮጌውን በር የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም መልሰው ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ ማያያዣዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።