ይሁን እንጂ በዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ወቅቱም ክረምት ነው፤ ስለዚህ ውጭ መቆም አንችልም፤ ከዚህም በላይ በዚህ ነገር ብዙ ኀጢአት ስለ ሠራን፣ ይህ ጕዳይ በአንድና በሁለት ቀን የሚያልቅ አይደለም።
ጉባኤውም ሁሉ እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድምፅ መለሱ፤ “እውነት ብለሃል፤ ያልኸውን መፈጸም ይገባናል።
ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋራ በተወሰነው ቀን ይምጡ።”