እነሆም፤ አጥፊ የሆነ የጦር መሣሪያ በእጃቸው የያዙ ስድስት ሰዎች በሰሜን አቅጣጫ ካለው ከላይኛው በር መጡ፤ ከእነርሱም ጋራ ቀጭን በፍታ የለበሰ፣ በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበ ሰው ነበር። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ገና አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በዚያ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር። ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ።
ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ።
ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ።
የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ አኖረው፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን መሥዋዕት በላዩ ላይ አቀረበ።
እነሆ፤ የሰሜን መንግሥታትን ሕዝቦች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ንጉሦቻቸው ይመጣሉ፤ ዙፋናቸውን በኢየሩሳሌም መግቢያ በሮች፣ በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ይዘረጋሉ።
የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤
የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ።
ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ ከሰሜን መቅሠፍትን፣ ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”
እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “በኪሩቤል ሥር ወዳሉት መንኰራኵሮች መካከል ግባ፤ በኪሩቤል መካከል ካለውም የእሳት ፍም እጅህን ሞልተህ ዝገን፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” አለው። ሰውየውም እያየሁት ገባ።
እርሱም እጅ መሳይ ዘርግቶ የራስ ጠጕሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ እርሱም ቅናት የሚያነሣው ጣዖት ወደ ቆመበት፣ ወደ ውስጠኛው አደባባይ መግቢያ ወደ ሰሜን በር ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ራእይ ወሰደኝ።
እነሆ በፍታ የለበሰውና በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበው ሰው ተመልሶ፣ “እንዳዘዝኸው ፈጽሜአለሁ” አለ።
በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤
ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰና በወገቡም ላይ የአፌዝ ወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ።
ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጸሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።
የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በሰውነቱ ላይ የሚያርፈውን ከበፍታ የተሠራውን የውስጥ ሱሪ ያጥልቅ፤ የበፍታውን መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የበፍታውን መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ ልብሶቹ የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ከመልበሱ በፊት ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ።
ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ ጕልላቶቹን ምታ፤ በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤ የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።
ሰባቱን መቅሠፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክት ከቤተ መቅደሱ ወጡ፤ እነርሱም ከተልባ እግር የተሠራ ንጹሕ የሚያበራ ልብስ ለብሰው፣ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ነበር።