Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 9:10

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም የሠሩትን ሥራ በራሳቸው ላይ እመልስባቸዋለሁ እንጂ በርኅራኄ ዐይን አላያቸውም፤ ከሚመጣባቸውም ነገር አላድናቸውም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፤ ለበደለኛው ስለ አድራጎቱ የእጁን ክፈል፤ ከበደል ነጻ ለሆነውም ንጽሕናውን ይፋ በማድረግ ይህንኑ አረጋግጥለት።

ከሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም። በደለኛውን፣ በደሉን በራሱ ላይ አድርገህ እንደ ሥራው በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ። ንጹሑም በደለኛ አለመሆኑን አስታውቅ፤ እንደ ንጽሕናውም ክፈለው።

ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።

“እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጧል፤ ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤ የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤

ባላጋሮቿ ገዦቿ ሆኑ፤ ጠላቶቿ ተመችቷቸዋል፤ ከኀጢአቷ ብዛት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ከባድ ሐዘን አምጥቶባታል። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው፣ ወደ ግዞት ሄደዋል።

ነገር ግን ልባቸው ወደ ረከሱ ምስሎቻቸውና ወደ ጸያፍ ተግባራቸው ያዘነበለውን እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

“ ‘በእነዚህ ነገሮች አስቈጣሽኝ እንጂ የልጅነትሽን ወራት አላሰብሽም፤ ስለዚህ የሥራሽን እከፍልሻለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በሌላው አስጸያፊ ተግባርሽ ሁሉ ላይ ዘማዊነትን አልጨመርሽምን?

“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕያውነቴ እምላለሁ ያቃለለውን መሐላዬንና ያፈረሰውን ኪዳኔን በራሱ ላይ አመጣለሁ።

ስለዚህ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ በጽኑ ቍጣዬም አነድዳቸዋለሁ፤ ያደረጉትንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

የሴሰኝነታችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ፤ ጣዖት በማምለክ ለፈጸማችሁት ኀጢአት ቅጣት ትሸከማላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”

“ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ የምሠራበትም ጊዜ ደርሷል፤ ወደ ኋላ አልልም፤ አልራራም፤ አላመነታምም። እንደ መንገድሽና እንደ ተግባርሽ ይፈረድብሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ራእይ የሚመስልና እንዲሁም በኮቦር ወንዝ ካየሁት ራእይ ጋራ የሚመሳሰል ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።

ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መቅደሴን በረከሱ ምስሎችሽና በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ስላጐደፍሽ፣ ፊቴን ከአንቺ እመልሳለሁ፤ በርኅራኄ አልመለከትሽም፤ አልምርሽም።

አሁንም መጨረሻሽ ደርሷል፤ ቍጣዬን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፤ እንደ አካሄድሽ እፈርድብሻለሁ፤ ስለ ጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ።

በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረትም አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’

ስለዚህ በቍጣ እመጣባቸዋለሁ፤ በርኅራኄ ዐይን አላያቸውም፤ ከሚመጣባቸው ነገር አላድናቸውም፤ ወደ ጆሮዬም ቢጮኹ አልሰማቸውም።”

እነሆ በፍታ የለበሰውና በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበው ሰው ተመልሶ፣ “እንዳዘዝኸው ፈጽሜአለሁ” አለ።

እኔም እየሰማሁ፣ ለሌሎቹ እንዲህ አለ፤ “በከተማዪቱ ሁሉ እርሱን ተከትላችሁ ግደሉ፤ ዐዘኔታና ርኅራኄ አታሳዩ፤ ግደሉ፤

የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።

“ጢሮስና ሲዶና እንዲሁም እናንተ የፍልስጥኤም ግዛቶች ሁሉ ሆይ፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ምን አላችሁ? ስላደረግሁት ነገር ብድር ልትመልሱልኝ ነውን? የምትመልሱልኝ ከሆነ፣ በፍጥነትና በችኰላ እናንተ ያደረጋችሁትን በራሳችሁ ላይ መልሼ አደርግባችኋለሁ።

ከእንግዲህ በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራምና” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ፤ እኔም ከእጃቸው አላድናቸውም።”

የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።

“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች