እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ጕልበት ሁሉ ውሃ ይሆናል።
ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።
የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህ በሕዝቤ ላይ፣ በእስራኤልም መሳፍንት ሁሉ ላይ መጥቷልና፤ ጩኸት፣ ዋይታም አሰማ። እነርሱ ከሕዝቤ ጋራ በአንድ ላይ፣ ለሰይፍ ተጥለዋል፤ ስለዚህ ደረትህን ምታ።
እነርሱም፣ ‘ለምን ታቃስታለህ?’ ቢሉህ፣ ‘ስለሚመጣው ክፉ ወሬ ነው፤ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅም ሁሉ ይዝላል፤ ነፍስ ሁሉ ይደክማል፤ ጕልበትም ሁሉ ውሃ ይሆናል’ በላቸው። እነሆ፤ ይመጣል፤ ይፈጸማልም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።
በዚያ ጊዜ ንጉሡ በድንጋጤ ተሞላ፤ ፊቱም ተለዋወጠ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጕልበቶቹም ተብረከረኩ።
ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ።