መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁም ይሰባበራሉ፤ የታረዱ ሰዎቻችሁን በጣዖቶቻችሁ ፊት እጥላለሁ።
መሠዊያውንም በእግዚአብሔር ቃል በመቃወም እንዲህ አለ፤ “አንተ መሠዊያ ሆይ! እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እነሆ፤ ኢዮስያስ የተባለ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ እርሱም አሁን እዚህ መሥዋዕት የሚያቀርቡትን የኰረብታ ማምለኪያ ካህናት በላይህ ይሠዋቸዋል፤ የሰዎችም ዐጥንት በአንተ ላይ ይነድዳል።’ ”
አሁንም ኢዮስያስ ማምለኪያ የድንጋይ ሐውልቶችን ሰባበረ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈራረጠ፤ ስፍራውንም በሞቱ ሰዎች ዐጥንት ሞላው።
ከእያንዳንዱም የይሁዳ ከተሞች የማምለኪያ ኰረብቶችንና የዕጣን መሠዊያዎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በርሱ አገዛዝ ዘመን ሰላም አገኘች።
ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣ እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቅቃቸው፣ የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣ በዚያ ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ ይህም ኀጢአቱ የመወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።
በግብጽ ምድር የሚገኙትን የፀሓይ አምላክ ቤተ ጣዖት ሐውልቶች ይሰባብራል፤ የግብጽንም አማልክት ቤተ ጣዖቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ”
ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል።
የታረዱት ሰዎቻቸው በመሠዊያው ዙሪያ በጣዖቶቻቸው መካከል፣ ከፍ ባሉ ኰረብቶች ሁሉና በተራሮች ዐናት ሁሉ ላይ፣ በለመለመ ዛፍ ሁሉና ቅጠሉ በበዛ ወርካ ሁሉ ሥር፣ በአጠቃላይ ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን ባቀረቡበት ስፍራ ሁሉ ተጥለው ሲታዩ፣ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
በሚቀጥለው ቀን ጧት ተነሥተው ሲመለከቱ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት፣ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆን፣ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።