Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 6:10

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ይህንም ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርሁት በከንቱ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሰይፍ አምልጠው፣ ከግብጽ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመለሱት በጣም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። በግብጽ ምድር ለመኖር የመጡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ፣ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማንኛችን ቃል እንደሚጸና ያውቃሉ።

ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ሳይዘገይ ይፈጸማል፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ፤ የተናገርሁትን ሁሉ በዘመናችሁ እፈጽማለሁ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።

“ከዚያም ቍጣዬ ይበርዳል፤ በእነርሱ ላይ የመጣው መቅሠፍቴ ይመለሳል፤ ስበቀላቸው እረካለሁ፤ በእነርሱም ላይ መዓቴን ካወረድሁ በኋላ፣ እኔ እግዚአብሔር በቅናት እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።

“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ቤት ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ጸያፍ ተግባራቸው ሁሉ የተነሣ በሰይፍ በራብና በቸነፈር ይወድቃሉና፤ በእጅህ እያጨበጨብህ በእግርህም መሬት እየረገጥህ፣ “ወየው!” ብለህ ጩኽ።

የታረዱ ሰዎቻችሁ በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።

ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ በእኛና በገዦቻችን ላይ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም።

ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች