Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 48:9

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የዚህ መባ ርዝመት ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ ስፋቱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ ‘ለካህናቱ ርስታቸው እኔ ብቻ ነኝ፤ በእስራኤል ምንም ዐይነት ርስት አትስጧቸው፤ እኔ ርስታቸው እሆናለሁ።

“ ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በዕጣ በምትከፋፈሉበት ጊዜ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ሺሕ ክንድ የሆነውን አንዱን ክፍል፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ አድርጋችሁ ስጡ፤ ስፍራውም በሙሉ ቅዱስ ይሆናል፤

ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል።

“ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

በከነዓን ምድር በሴሎም፣ “እግዚአብሔር የምንኖርባቸውን ከተሞች፣ ከብቶቻችን ከሚሰማሩባቸው ቦታዎች እንድትሰጡን በሙሴ በኩል አዝዞልን ነበር” አላቸው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች