በምሥራቅ በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የዮሴፍ በር፣ የብንያም በርና የዳን በር ናቸው።
“የከተማዪቱ መውጫ በሮች እነዚህ ናቸው፤ “ከሰሜን በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ካለው በር አንሥቶ፣
የከተማዪቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ያሉት ሦስቱ በሮች የሮቤል ነገድ በር፣ የይሁዳ ነገድ በርና የሌዊ ነገድ በር ይሆናሉ።
በደቡብ በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች አሉ፤ እነዚህም የስምዖን በር፣ የይሳኮር በርና የዛብሎን በር ናቸው።