ምድሪቱን የሚያርሱ የከተማዪቱ ሠራተኞች ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ይመጣሉ።
“ ‘ከተቀደሰው ስፍራ ጋራ የተያያዘ ወርዱ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ የሆነ ቦታ ለከተማዪቱ ርስት አድርገህ ስጥ፤ ይህም ለመላው የእስራኤል ቤት ይሆናል።
ከዚህ የሚቀረው፣ የተቀደሰውን ክፍል የሚያዋስነውና በተጓዳኝ ያለው ቦታ በምሥራቅ ዐሥር ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። ምርቱም ለከተማዪቱ ሠራተኞች ምግብ ይሆናል።
አጠቃላይ ይዞታው በአራቱም ማእዘን እኩል ሲሆን፣ እያንዳንዱ ማእዘን ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከከተማዪቱ ድርሻ ጋራ የተቀደሰውን ክፍል ልዩ መባ በማድረግ ታስቀምጣላችሁ።