እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ ውሃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይፈስሳል፤ ወደ ባሕሩ ወደሚገባበት ወደ ዓረባ ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ሲፈስስ፣ በዚያ የነበረው ውሃ ንጹሕ ይሆናል።
ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔር አንዲት ዛፍ አሳየው፤ ዕንጨቷንም ወደ ውሃው ጣላት፤ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ። በዚያም እግዚአብሔር ሕግና ሥርዐት አበጀላቸው፤ በዚያም ስፍራ ፈተናቸው።
ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል።
ዐንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፤ የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል፤ ውሃ ከበረሓ ይወጣል፤ ምንጮችም ከምድረ በዳ ይፈልቃሉ።
ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤ የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል። ቀበሮዎች በተኙባቸው ጕድጓዶች፣ ሣር፣ ሸንበቆና ደንገል ይበቅልበታል።
የምድረ በዳ አራዊት፣ ቀበሮና ጕጕት ያከብሩኛል፤ በምድረ በዳ ውሃ፣ በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና። ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤
የተማረኩትን፣ ‘ኑ ውጡ’ በጨለማ ያሉትን፣ ‘ነጻ ሁኑ!’ እንድትል አድርጌሃለሁ። “በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤ በተራቈተውም ኰረብታ ሁሉ ላይ መሰማሪያ ያገኛሉ።
እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሕዝቡ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሯቸውም አይሰማም፤ እንዳያዩም ዐይናቸውን ጨፍነዋል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው፣ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኋቸው ነበር።’
ዐልፎ ዐልፎ የጌታ መልአክ ወርዶ ውሃውን በሚያናውጥበት ጊዜ፣ ቀድሞ ወደ መጠመቂያዪቱ የገባ ካደረበት ማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።]
የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።
በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን ዓረባን በሙሉና ከፈስጋ ተረተር በታች ያለውን የዓረባ ባሕር ያጠቃልላል።
ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።