እንደ ገናም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ አሁን ግን ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ ምክንያቱም ውሃው ስለ ሞላና ጥልቅ ስለ ነበረ፣ በዋና ካልሆነ በቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ነበረ።
በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
ቀጥሎም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ጕልበት ወደሚደርስም ውሃ መራኝ፤ ከዚያም ሌላ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ወገብ ወደሚደርስም ውሃ መራኝ።
ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን ሁሉ፣ ምድርም የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።
ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”
ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር።